Refusal decision of the Holy synod members of Ethiopian orthodox church about Reformist/Tehadiso/Hara tiqa/ service in the name of the church

አሁን እነዚህን አባቶቻችንን ምን እንበላቸው???
የዚህ ጽሑፍ ዋና ዓላማ ልጆቻቸውን በትዕግስት ሰምተው፣ እውነትነትን አጣርተው፣ የእግዚአብሔርን ፍቃድና ፍርድ ለቤተክርስቲያን ያስተላለፉትን የዘመናችንን ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ክቡራን አባቶቻችንን ማበርታትና በዚህም በረከታቸውን ማግኘት ነው፡፡
አሁን ያለንበት ዘመን በጎ አይሉት ክፉ፣ ክፉ አይሉት በጎ ሆነና ብዙ ይነገራል፣ ብዙ ይሰማል፣ ብዙ ይጻፋል፣ ብዙ ይነበባል፣ ብዙ ይታያል ጥቂቱን ግን እንመለከተዋለን፡፡ በተለይም በዚህ ዘመን ላይ ላለን ትውልዶች ፈተናም ካወቅንበት መልካም አጋጣሚም የሚሆኑ በርካታ ነገሮች(ክስተቶች) አሉ፡፡ ለዛሬው ግን የተሃድሶን ስልትና እንቅስቃሴን ማሰቡ በቂያችን ነው፡፡ ምክንያቱም በዚህ አንድ ዘመኑ ክስተት
·         ብዙዎች ተጠቅመዋል፡፡
1.      በመንፈሳዊ ምዘና ሲታይ አባቶቻችን ከቀድሞው እስከ አሁን በውሳኔያቸው፣ በተለይም በሰሞኑን የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ፍሬው ያማረ ውሳኔ፤ አገልጋዮቻች ብዙዎች እንዲነቁ ተግተው ሰርተዋል፤ በጽሑፍ፣ በስብከት፣ በጸሎት፣ በክርክርም፣ በውግዘትም ሳይቀር የሚችሉትን ለማድረግ ወስነዋል…. ስለዚህም ተጠቅመዋል፡፡
2.     በስጋዊና  ግዑዝ በሆነ ምዘና ደግሞ በገንዘብና ተከታይ ድሆች የነበሩ አሁን ቢጠሯቸው አይሰሙም፣ ታዋቂ ያልነበሩ ለብዙዎች መውደቅና መሳት ምክንያት ሆነዋል ባይዘልቅም እስካሁን ግን ብዙ ደጋፊና ወዳጅ አፍርተዋል፡፡ከሞትህ በፊት እኔ ልሙት የሚሉ ባለማስተዋል የሚንቀሳቀሱ አጃቢዎችን አፍርተዋል፤ የሚበዙትም በስደት የሚገኙ ምዕመናን ናቸው፡፡
§  እናታችንን በእጅ አዙር መቆራኘት ሲሹ የኖሩ አካላት ወጣ ገባ እያሉም ቢሆን ተሳክቶላቸዋል፡፡
§  ሌላ በጎ ያልሆነና ጎዶሎ የኑሮ ስርዓት (ርዕዮት) የሚሰብኩና መኖር የሚፈልጉም ቢሆኑ ድምፅዋን እንዳሻችው እንዳታሰማ አድርገዋታል፡፡በዚህም እነሱ ደጋፊዎችን እናታችን ደግሞ አላዋቂ ነቃፊዎችን አትርፋለች፡፡ ለዚህም መነሻቸው
·         የቤተክርስቲያንን ዓላማና አስተምሮዋን ባለመረዳት ምክንያት፡- ምሳሌ ስለ በዓላት ያለው አስተምሮ(ዋጋው ሰማያዊ ስለሆነ በምድር ሊተው የሚገባ ነገር እንዳለና ለሁሉም መጠን እንዳለው እናታችን ታስተምራለች) የሚገርመው ግን ይህ ርዕዮት የሚከተሉ ሰዎች ስለ አቀንቃኞቹ ስህተት መናገር አይፈልጉም ምክንያቱም በበዓላት ቁጥር አከባበር እነሱ የባሱ ስለሆኑ ይሆናል
·         አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ሆን ብለው የማትለውን ትላለች በማለት ስለ ግርዛት፣ ስለስራ መስራት፣ ስለ እኩልነት…ወ.ዘ.ተ. በተሳሳተ መንገድ ስለተረዷት የሚሰብኩት ነው፡፡
3.     በሰይጣናዊ ምዘና ሲታይ ብዙ የእምነት ጠባይ እንኳ የሌላቸውን በጎች እንዲያገኙ አድርጓል፡፡ በጀማሪዎቻቸው ሳይቀር የተናቁ መነሻቸው ስጋ መድረሻቸው ሲዖል የሆኑ በርካታ የአዳራሽ አስጯሂዎች ዛሬ ዕድሜ ለተሃድሶ ይላሉ የማትደፈረዋን አስደፈረን የማትነካዋን አስነካን እናም በርካታ የሲዖል አጯጯሂ አግኝተዋልና ነው፡፡ ግን እኔ ይህን አምናለሁ ከእኛ የሆኑ ቢሄዱም ይመለሳሉ (ሄደው ከሚቀሩት መካከል የእኛ የሆነ የለም፣ እኛ ከሆናችሁ ግን ንቁም ተመለሱም) ምክንያቱም 1ኛ ዩሐ 2፡19 ከእኛ ዘንድ ወጡ  ዳሩ ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ከእኛ ጋር ፀንተው በኖሩ ነበር ነገገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ ይገለጡ ዘንድ ወጡ፡፡


·         ብዙዎች ተጎድተዋል፡፡
1.      በተለይም ያልጠለቀ ስር ያላቸው ተክሎች የሚመሰሉ ምዕመናን የተኩላ ድምጽ ተከትለው ነጉደዋልና በብዙ ተጎድተዋል፡፡ እርግጠኛ ነኝ ተኩላው አንድ ቀን ጥርሱን ማሳየቱ ስለማይቀር ተስፋ አደርጋለው በግ አለመሆኑን ይረዱታል፡፡ እንዲህም እንዲሉ ሰማያዊ አባታችን እግዚአብሔር ይፈቀድላቸው በእነሱ መመለስ ለመዘመር ያብቃን! አሜን፡፡
2.     መልክ፣ ቁመና፣ ቃላት፣ ገንዘብ ስልጣንን አይተውን ፈርተዉ ተኩላን ተኩላነቱን አውቀው ያልመሰከሩ የበጎ ቀን ብቻ አገልጋዮች ይጎዱበታል በፈተና ወድቀዋልና፡፡
3.     ዓላማዋን ገልብጠው የሚያነቡና የሚያስነብቡ እንሰሳ ብቻ የሆኑ ሰዎች በብዙ ተጎድተዋል፣ ይህ ማለት ሰማይና ምድርን እንዳለመለየት ነው፣ እናታችን ሰማያዊ ስራን እሰራች ሳለች የምድርን ስሪ ማለት መታለል ነው፡፡ ጊዜውን ባናውቅም እንደ አባታቸው ናቡከደነጾር ሳር(አሳር) መብላታቸው አይቀርም፡፡ ይህ እንዳይሆን እናቴ ሁል ጊዜ ስትጸል እሰማታለሁ፡፡(በእንተ ቅድሳት)
ይህን ሁሉ ያስባለኝ ግን የበጉንም ሆነ የተኩላውን ጥርስ እንድቆጥርና እንድናውቅ ስላሰለጠኑን፣ ስለሚያሰለጥኑን በጥበበ እግዚአብሔር ዛሬም ቆጥረው አስረከቡን፡፡ በዚህ ጉባዔ ማን የማን ልጅ እንደሆነ ማንስ የማን ምላስ እንደሆነ ሊያስታውቁን ልዩ በሆነና ቋሚ አባላት ባሉት ጸረ ተሃድሶ ኮሚቴ ስራውን ሊጀምር በሙሉ ድምጽ በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጸድቋል፡፡ይህ አካል በስሟ የሚነግዱ ለክብራቸውና ለሆዳቸው የሚሰሩ አገልጋዮችን ካሉበት ገብተው ይከራከራሉ፣ ይመክርሉ፣ መንገድ ያሳያሉ፣ አሻፈረኝ የሚሉ ሲኖሩም ስሟን ከልክላ ከዓውደ ምህረቷ ታሰናብታለች፡፡ አባቱን የማያከብር ልጅ እድሜው አጭር ነው፡፡
በዚህ የአባቶች ስብሰባም ሌባን ሌባ ማለት ተገቢ መሆኑን ተረድቼበታለሁ፣ ምክንያቱም ሌባው እኔ ሌባ ነኝ ሊልም አይችልም ብሎም አያውቅም፡፡ አርዮስም እንኳ ቢሆን አባቶቹ ና አባቶቻችን አንተ አላዋቂ ነህ፣ ከሀዲ ነህ ልትወገዝ ይገባል አሉት እንጂ እሱ ራሱ እኔ ከፍሌ አማኝ ነኝ፣ አውግዙኝ ሲል ሰምተን አናውቅም፣ ሌሎችም መናፍቃን መንገዳቸው ይሄ ነው ሌላ መንገድ የለም፡፡ በምክሩ የበታችነቱን አውቆ የሚመለስ ሲኖር ሌላው ደግሞ እልህ ገብቶት፣ ለምን ተነካው፣ እኔ እኮ ተዓምራት እሰራለሁ፣ ታዋቂ አገልጋይ ነኝ፣ እንዴት ልክ አይደለህም እባላለው የሚል ጅል ሰው አለ ይህም ከግንዱ የተጣላ ቅርንጫፍን ይሆናል፣ ግንዱ ሌላ ቅርንጫፍ ያወጣል ቅርንጫፉ ግን ፍሬ የማፍራት ተስፋውን ያጣል፡፡ ዩሐ 15፡1
አባቶቻችን ይህን ማድረጋችሁ ኃላፊነታችሁ ቢሆንም ብዙ ጓጉተንለት ስላገኘነው ደስ ብሎናል፣ መጨረሻውን ያሳየን፣ እግዚአብሔር ያጽናችሁ፣ በረከታችሁና ጸሎታችሁም ትድረሰን፡፡

ስማችሁን ግን መጨረሻውን ካየን በኋላ እናወጣለን!!!
እናመስግናችኋለን፡፡ ይቆየን!

አምላከ ቅዱሳን ከክፉ ይጠብቀን!! አሜን



Comments

Popular posts from this blog

እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክረስቶስ የልደት በዓል አደረሰን አደረሳችሁ!!!