ይድረስ፤ ለሰማዕታት፣ ለአባቶችና ለቄሳሮቻችን
ይድረስ ለእናንተ
ሰማዕታት
ለጤናችሁ
እንደምን አላችሁ እንዳልል ሰላም ከሌለበት ዓለም በሰላም አባት ክርስቶስ መጠራታችሁን መሪዎቻችንና አባቶቻችን በይፋና በፍጥነት
ባይነግሩንም ጠላቶቻችን ገዳዮችና ባዕዳኖች የተባሉ መገናኛ ብዙሃን ነግረውናል፡፡ እናንተየ አዲሱ ቤታችሁ እንዴት ያምር? እንዴት
ይደንቅ ይሆን? እንዴትስ የሚያብረቀርቅ የተወደደና የተለየ ዘላቂ ማረፊያ አግኛታችሁ ይሆን? እኔ ምለው ሰማዕታት
ለመሆኑ
ማነው ያስተማራችሁ?
ማነው ያጠመቃችሁ?
ማነው ያሳመናችሁ?
ማንስ ነው የሰማዕትነትን ዋጋና ጣዕም ያቀመሳችሁ?
ማንስ ነው ዘመኑን አትምሰሉ፣ ወደኋላ አትበሉ፣ የሎጥን ሚስጥ ታሪክ
አስታውሱ ያላችሁ?
ማንስ ቄስ ፣ ማንስ ጳጳስ ትጉ በርቱ ጽኑ ብሎ ቡራኬ ሰጣችሁ?
የትስ ኮሌጅ ፣የት ዩኒቨርስቲ የመንፈስ መበርታትን የዓላማ ፅናትን ተማራችሁ
…….. ? መልሱን ለውሳጣዊ ነፍሴ መልሱላት(አማልዱኝ)፡፡ እኔ ግን እላለሁ
እናንተ ሰማዕታት ንዑዳን ናችሁ, ገንዘብ ብላችሁ ሄዳችሁ
ሐይማኖት ገዝታችሁ መጣችሁ, ላንረሳ በልባችን ተፃፈ ስማችሁ
እናንተ ሰማዕታት ክቡራን ናችሁ, ኢትዬጵያ ሀገረ እግዚአብሔር
መሆኗን ለዓለም መሰከራችሁ፡፡
እናንተ ሰማዕታት ታላላቆች ናችሁ የእህታችንን ግብፅ ዋጋ
ወደ እኛም አደረሳችሁ፡፡
ሰማዕታት ወንድሞች ሆይ
ወዮ ለእኔ
ወዮ ለእኔ ወዮዮዮዮዮዮዮ……
ብዬ ባለቅስ ወደድኩ ጥቁር ገጀራ አስፈሪ ሽጉጥና መሳሪያ እያሳየዋችሁ
ሰው መሳይ ሰይጣኖች ከበዋችሁ ጭው ያለ በርሃ ውሃ ምግብ ከልክለዋችሁ ቤተሰቦቻችሁን ከእናንተ የሚጠበቅ ብዙ ውለታ እንዳለ እያሰባችሁ
እያወቃችሁ እንዴት ---- እረ እንዴት አስቻላሁ
በእርጋታ መንፈስ ዝም አላችሁ፡፡
እኔስ እላለሁ
ሰማዕታት
ሆይ የእናንተ በረከት እጥፍ ይሁንልን
የቀረነውን
እኛን ያፀናን ለምኑልን
የኤልያስ
ለኤልሳዕ እንደሆነው ለእኛም ይሁንልን
ሰማዕታት
ወንድሞቻችን ሆይ ምክራችሁ ፀሎታችሁ ፅናታችሁን እንዴት አድርገን
ገንዘብ
እናደርግ እንዴትስ አድርገን እናግኘው ወዮ ……….
አባቶች
ምዕመኖቿን
የማታውቁ ይመስል የቄሳርን አባባል በመግላጫቹ ያሰማችሁን የቀደሞው ኩራታችሁ ወዴት ተሰወረባችሁ፡፡እረ ወዴት ወዴት እራቃችሁ….. አባቶቻችን
ሆይ ለሐይማኖት ጀግና የሆኑትን ንድታከብሯቸው ከእግዚአብሔር በቀር ሰው ይነግራችሁ ዘንድ ለምን በጀ አላችሁ? ሞትኮ አይቀርም መጠየቅ
እኮ አይቀርም ከእናንተ የምንጠብቀውን ከእኛ መጠበቅ ከሆነ ስራችሁ እኔስ እላለሁ ወዮውላች፡፡
በጐችን
ትጠብቁ ዘንድ የተቀበላችሁትን ፀጋ የት አደረሳችሁት ማፅናናታችሁ ማበርታታችሁ ከዓለም ልዩ መሆናችሁስ ወዴት አለ? እስኪ ተማልከቱ
ሳይማሩ ያስተማሩንን ውድ ሰማዕታትን እናከራቸው ዘንድ ይገባል
በቃል የሚያውቁትን በተግባር ለገለጡልን ሰማዕታት ክብር ይገባል
የቀደመውን የአባቶች ፍሬ ለእኛ ያበረከቱትን በዘመናችን
ያሳዩን ሰማዕታት ማወደስ ይገባል
ምን አላችሁ ስትሰሙ?
ስታዩ
?
እውነት ነው በጐች እረኞቻቸው ባይጠብቋቸውም ባያሰማሯቸውም እንኳን ይኖራሉ, ምክንያቱም የሰማይ ዘላለማዊ እረኛቸው
አለና፤ --- በቃ ልክ እንደዚህ በተግባር የሞቱ ሰማዕታትን ሳያዩ፣ ምን አልባትም
በደምብ ሳያውቁ በሙሉ ተስፋ መወሰድ በክብረ ሰማዕታት መማረክ ችለዋልና እናንተስ ምን አላችሁ…..
እውነት ነው አባቶቼ እናንተ አስተዋይ መሆን አለባችሁ
ግን ወላዋይ ደግሞ እንዳትሆኑ ከአስተዋላችሁ፡፡
የምትጠብቁት እኛን በጐችን ብቻ አለመሆኑን ከተረዳችሁ
እኔ አምናለሁ ራሳችሁንም ትጠብቃላችሁ
ይሆናልና ርትዕ ሁሉም ውሳኔያችሁ
በሉ አባቶች
ዘመኑ የሰማዕትነት ነውና እወቁበት፣ በጎች በረት ገብተው እረኞች ቤት እንዳይጠፋቸው! አሁን በርቱልን አበረታቱን፡፡
ቄሳሮቻችን
ባለስልጣናት
ወዴት አላችሁ ጥቂት ስለእናንተ ማውራት ብዙ ከማውራት ይከብዳል፡፡ በርካታ ጊዜ በደላችሁ የአሁኑ ግን ባሰ ወንድሙን የማያውቅ፣
ሕዝቡን የማያውቅ ….. መሪ ነኝ ባይ በዛ በማይከፈልበት የመስታወት መስኮት ብቅ ብሎ ለዓለም የገረመ ጥርጣሬን ነገረን ዘራብን
ቆይ ላጣራ የእኛ አይመሱልኝም አለን፡፡
እረ መቼ
ይሆን ኢትዮጵያዊ መሪ የምትሆኑት መልካችንን ደማችንን መከራችንን ሐሳባችንን ጥረታችንን የምትረዱትና የምትረዱን?
ይህ ያላችሁት
እኮ ገዳያችን ISIS እንኳን አላለውም፡፡ አስተውሉ እንጂ እንዴት እንዲ ይባላል? አሁን ኢትዮጵያ ያውም በአሁኑ ጊዜ የሞቱን ሰዎች
ማጣራት ትችላለች? ማወቅስ ትችላለች? እንዴት ልታደረጉ ነበር ያሰባችሁት ግብጽ ኤምባሲ ለመደወልና ለመጠየቅ በኢቢሲ ቆይ ማለት
ይጠይቃል?
ስለ እናንተ
ስንል ምን እንሁን አስተዋይ መሪ ጠፋ
ተመሪው
መሪውን መራ ታዲያ ምን ይበጅ?
ዓለም
እንዲስቅባችሁ ለምን ፈቀዳችሁ የእኛ መሆናቸውን ሁሉ ሲያረጋግጥ እናንተ ብቻ እናጣራ አላችሁ ያውም 24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ አጣራን
ብላችሁ ዘፈን እየጋበዛችሁን ዋላችሁ፣ ማታም ያው ለወሬ የኢትዮጵያውያንን ሐዘን ልብስ አንኳን ሳትለብሱ፣ የሐዘን አገላለጥ ጠፍቶባችሁ፣
የእኛ ናቸው አላችሁ፡፡ መቼስ ምን እንላለን የሚመሩን
-
እነማ እንደሆኑ እናውቃለን
-
ምን ሐሳብ እንዳላቸውም እናውቃለን
-
ሐይማኖት ሐገር እንደሌላቸው እናውቃለን
-
ስለሐይማኖት የማይገባቸውና የማያገባቸው እናውቃለን
-
Secularism እንዳልገባቸውም እናውቃለን
-
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ ማለት እንኳን እንደሚያሳፍራቸው እናውቃለን
-
መንፈሳዊነት ከስልጣን ጋር ግንኙነት የለውም እንደሚሉም እናውቃለን….
ግን
ይህን ያደረገና ያሳየን ደግሞ ሌላ ማድረግ አይሳነውምና ፍርዱን ከእሱ
እንጠብቃለን፡፡
አሁን
እናነተ መራችሁን ወይስ አማረራችሁን፣ ….ምን ይሰማችኋል
ISIS አባላትና
ደጋፊዎች
እጅግ እናመሰግናለን የሚያበረታ የሚያፅናና የሚያፀና
ቪዲዮ ማንነታቸውን ጨምራችሁ ገሀድ ስላደረጋችሁ
ከምንም በላይ በእናንተ ደስ ይለኛል ለዚህ ሁሉ ነፍስ መዳን
ምክንያት
ሆናችኋልና
ግን ደግሞ
ይከፋኛል ይህን ጣዕሙና ሽታው
ከምዕራብ እስከ ምስራቅ
ከደቡብም እስከ ሰሜን
የሚያውደውን ክርስትናን ሳትቀበሉ ብትሞቱ
በሕይወት
እስካለው አዝንላችኋለሁ ደግሞም እፀልያለሁ
እግዚአብሔርም
አያድርግባችሁ
F
ደማችሁን ሳትታጠቡ
F
ከምስጢር ሳትካፈሉ
F
የዚህን ፍቅር ምስጢር ሳትረዱ
F
የመጣችሁበትን ሳትረግሙ ፈፅሞ ፈጽሞ አይጥራችሁ
F ቸር አምላክ
ለንስሀ ሞት ያብቃችሁ፡፡
አሜን ይቆየን!!!
12,08,2007
Comments