የሀና ደፋሪዎች ከየት መጡ!?
የሚከተሉት ሰዎች እህታችንን የምድር ቆይታዋን
ቀጩባት ያሳዝናል፡፡ ሀና ፍርድ በዚያ አለ፣ እውነት በዚያ አለ፣ አምላካችንም መልክ፣ ስልጣን፣ ቁመና፣ ገንዘብ፣ ዝና …. ሌሎችም ሁሉ ለፍርዱ
የማይጠቀም ነውና ፍርድ ታገኛለሽ፡፡ ይሁን እንጂ እኚህ ክፉ አውሬዎች ጨከኞችና ከሀዲዎች ያደረሱብሽን ባልናገር ከበደኝ እናም ላጋልጣቸው
ተነሳው፡፡
እኔ ምለው አንተ አንባቢ ደሞ ለምን፣ ማን፣ እንዴት
ተደፈረች ትላለህ/ሽ/? አታፍርም እንደማያውቅ ሰው ታስመስላለህ? ግፍ አይሆንብህም፣ ህሊና አልህ ግን? ስማኝ ልጠቁምህ ሀናን የደፈራትን ያዋረዳትን ያን ሰው መሰል
ፍጡር፣ ሰው ነኝ ባይ ፍጡር አውቀዋለሁ/አውቃቸዋለሁ/ አውቅሃለው፡፡
እኔ ግን እላለሁ እነዚህ ደፋሪዎችና ሰው ብቻ
ሳይሆን እንሰሳም መሆን ያቃታቸው፣ ኢትዮጰያዊ ያውም ጎረቤቶቻችን እነ እንትና/እነ እገሌ/ ናቸው፡፡ ለማስለፍለፍ ፈልጋችሁ ካልሆነ
እናንተ አንባቢያኖች ሁላችሁም ታውቓቸዋላችሁ እረ እንደውም እናንተም ራሳችሁ ተባባሪ ነበራችሁ አውቃሁ፡፡
የማላውቅ መስሏችሁ እንጂ አውቃለሁ፣
ያልሰማው መስሏችሁ እንጂ ሰምቻለው፣
ያላየው መስሏችሁ እንጂ አይቻለው፡፡
መቼስ የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያድርቅ አይደል
የሚባለው፤
ከዘበዘባችሁኝማ አውነቱን ላወጣ ነው፣ እውነተኛ
ዳኛ ይዳኘን ብዬ፡፡ ለነገሩ ፍርዱም የተበላ ዕቁብ ሆኗል አሉ፣ ራስን የማያውቅ ዳኞች ናችሁ አሉ፣ እውነትን ሳይሆን ክብርን፣ ገንዘብን፣
መወደድን፣ ስልጣንን….. የምታሯሩጡ ቀማኛ ናችሁ አሉ፡፡ እናም ልንገራችሁ እንጂ እናንተስ ፍርድ አታውቁም፣ ፍርዳችሁም ኦርዮን
እንዲገደል መሆኑን አውቃለሁ፡፡አይ አንተ ኦርዮን ሚስትህንም፣ ፍቅርህንም፣ ህይወትህንም የተነጠክ ምንኛ ፍርድ ተጓደለብህ??? ፍርድ አውቃለሁ ካልክ አሁን የምነግርህ እውነት መሆኑን ታውቃለህ፣
አልያ አንተ ስለፍርድህ መጓደል እንደ ዳዊት ቅጣት ይጠብቅሃል፣ ካወክ ንስሃ ግባ፡፡
ትሰማላችሁ የእህቴ ገዳዮች እኛ ነን እኛ ራሳችን
እኛ፤
·
እኔ ራሴና፣ አንተ ነን፡፡አልገደልኩም እንዳትል እውነቴን
ነው ገለሃል፡፡እኔስ፣የእኔስ ጓደኛ፣እኔስ ቤተሰብ ለመንፈሳዊነት፣ ሰውን(እህቶቻችንን) ለማክበር፣ ለመውደድ ምን ያህል ነን? ምንም አንተስ ብትሆን መንገድ ላይ የማታሳልፍ፣ ጸያፍ ተናጋሪ፣
የምታየውን፣ የምትውልበትን የማታውቅ፣ የማይገባህን ሰሪ፣ …… አይደለህም? አንተስ በትሆን የሆነውን ጓደኛህን ምን መክረኸዋል? ምንም ደሞ ምን ትላለህ አንተ የምታየውስ የአባቶችህ መንገድና ህይወት ወይስ የረከሰ
የዝሙት ቀረጻ? የምትውለውስ በስራ ተጠምደህ ወይስ…..? መልሱን አንተ ታውቀዋለህ፡፡
·
መንግስት ነው፡፡ አልገደልኩም
እንዳትል ገለሃል/ገላችኋል፡፡ አይ ዴሞክራሲ፣ አይ ልማት፣…… ሰው ሳይለማ አእምሮው ዘቅጦ የሚመጣ
ልማት ውጤቱ ይህ ነው? አዎ ሀይማኖትን
መንፈሳዊትን ሰው ማክበርን ለትውልዱ እንዲማር አድርገሃል ወይስ ምድራዊ፣ሀይማኖት አልባ ተስፋቢስ/ምጸአትን ማያስብ/ እንዲሆን አደረከው?
·
የሀይማኖት አባቶች፣ ወንድሞችና
እህቶች ናችሁ፡፡ ጊዜ ጠቧችሁ መንገድ አታችሁ፣ ጉልበት አንሷችሁ፣ በጎች ፍለጋ ርቃችሁ ሔዳችሁ፣ በጎች አልጠበቅ ብለዋችሁ በጎቹን፣
ጠቦቶቹን፣ ግልገሎቹን በለመለመ መስክ ሳትጠብቁ ቀራችሁ? አይደለም
·
አንቺ ነሽ አልገደልኩም አትበይ
ገድልሻል፡፡ ግራ ገብቶሽ መንገድ ጠፍቶሽ ሱሪ ቀሚስ ቀሚስ ሱሪ ሆነብሽ አንቺ አልገደልኩም ገዳይዋ ይውጣ ስትይ አይከብድሽም? ስርዓት አታውቂ፣ ወይ አጠይቂ፣ ሲንግሩሽ አሰሚ፣ ወይ አትቀስሚ፡፡
እንዲሁ የውሃ ላይ ኩበት ሆነሽ አለሽ፡፡ አንቺ ይህንስ ልላስ ቀድሞ ባማረ ቃል አልተስበክሺምን? አንቺ ተለወጥሽ ጓደኛሽንስ ለወጥሽ፣ ለማይረባ ምኞት እህትሽን አሳልፈሽ አልሰጠሸም፣ የማይገባ
ቦታ ይዘሻት አልሄድሽም፣መጥፎ ልምድ አላስጀመርሻትም? አንቺ መልሺው፡፡
·
ነጋዴውም፣ መምህሩም፣ ሽማግሌዎችም፣
ህጻናትም ገላችኋታል፡፡ አኣአኣኣኣኣኣአኣአአ አይ ዌ ለእኔ ብለህ የማታስብ መሆንህን፣ ብር ፈላጊ መንፈሳዊነት የሌለው ስራ አልስራህም? አሽሽ ቤቱን፣ሲጋራ ማጨሻ፣ ጫት መቃሚያ፣ ዝሙት መስሪያ/መዳሪያ/ ቤቱን ማን
ከፈተው ማን አከራየው????? አንተ ነጋዴ ራስህ ሽማግሌዎቻችን
በቁጥር ብታንሱም ማንን መከራችሁ፣ ማንን መለሳችሁ፣ ማንን አስታረቃችሁ … ወይስ የቢራ አንገት ያዛችሁ? መልሱን ታውቁታላችሁ፡፡ አይ ህጻናት እናንተስ የሚጠቅማችሁን
ያዛችሁ ይሆንን፣ መንፈሳዊ ሆናችሁን፣ ሰውን አክባሪ ስርዓት አዋቂ/ጠያቂ/
ሆናችሁን፣ ወይስ ባማታውቁት ቋንቋ ምን ሰማችሁ ምን አላችሁ ምንስ አያችሁ? ለቤተሰባችሁ ንገሯቸው፡፡
·
ተመራማሪው፣ ተማሪውም፣ እናትም፣
አባትም ገላችኋታል፡፡ ተመራምረህ ነበር እንዴ፣ ህዝብን የሚጠቅም፣ ችግርን የሚያስወግድ፣ አስተሳሰብን የሚያሻሽል ግኝት አልህ? እንደው ገንዘብ አሳዳጅ እውነት የማታውቅ ሆነሃል? መልሱን ተመራምረህ አግኘው፡፡ ልጆችን እንዴት አሳደጋችሁ ይሆን
በስርዓት በሕግ በሀይማኖት ወይስ እንዴት? እናንተው መልሱት፡፡
እውነቱ ይህ ነው፣ እውነት እንፍረድ!!!
Comments