መናፍቅም ድሮ ቀረ ልጄ???
መናፍቅም ድሮ ቀረ ልጄ???
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
አሀዱ አምላክ አሜን!
እኔ ግን እላሉሁ
·
ስም ድሮ ቀረ!
እነ እሱያውቃል፣ ተስፋነሽ፣ ግሩም፣ እጹብድንቅ፣ ተመስገን፣ …. እረ ስንቱ
ምንጥ ስም እንሰማ ነበር አሁንማ ምን ስም አለ….(ያለ ምክንያት ቲቲ ዳዲ ሪች…. ከመባል ውጭ)፡፡
·
ምግብ ድሮ ቀረ፣ መዝናናት ድሮ ቀረ፣ ምንኩስና ድሮ ቀረ፣ ብሕትውና ድሮ ቀረ፣ አባትነትም እናትነትም
ድሮ ቀረ፣ መምሕርነት፣ ተማሪነት፣ መሪነት ተመሪነት ሁሉም ተያይዘው ድሮ ቀሩ …. (በቃ ሁሉም ድሮ ቀረ ብለው በባሕል፣ በወግ
መጣስና መጠበቅ አለመቻል ሆድ እየባሳቸው አንድ ሊቅ ነገሩኝ)፡፡
·
ሌላው ቀርቶ ለማኝነትም ድሮ ቀረ …አሁንም ፈሽን ተከታይ ለማኝ ሀገሪቷን ወሯት አይታይህም አሉኝ፡፡
... ምን ማለትዎ ነው ስላቸው እነዲህ አሉኝ እስኪ ስማው
የሚለምንበት አላማን
የሚለምንበት ስምና መንገድ
ልመናውን ጨርሶ ሲሳካለት የሚያመሰግንበት
መንገድና ቃላት…. (እኮ ፍጹም ኢትዮጵያዊውም ሃይማኖታዊም ሽታ የላቸውም… ዝርዝሩን ለአንተ አሉኝ)፡፡
·
ግን እኮ….. መናፍቅም ድሮ ቀረ ብለውኝ እርፍ አሉ፡፡ እናንተ ለካ መናፍቅ/ ኢ አማኒም የለም/
አሉኝ …… ወቸ ጉድ ብለው እኛን በክርክር አላስወጣ አላስገባ ያለንን ይህንን ሁሉ መሰረተ ቢስ መናፍቅ ወዴት ዘነጉት እንድል አደረገኝ፡፡ ለነገሩ አሉኝ እግዚአብሔር ላያስችል አይሰጥም
ይባላል አሉኝና የተለመደውን ምሳሌያዊ ንግግር ጣል አደረጉቢኝ… በእውነቱ እንዲህ ያለ ተመስጦ ውስጥ ሆኜ የሰማሁት ሰው በዘመኔ
በጣት የሚቆጠሩ ናቸው፡፡ ወደኋላ ማሰብ እንድችል በጠቀስኩላችሁ ሁሉ በእምዬ እገሌ ጊዜ እኮ እያሉ በቃ ምን ልበላችሁ አስታቀፉኝ
አጠገቡኝ ግን ምን ያደርጋል እሳት አመድ ወለደ ሆነና ስጋ እንዳማረን ቀረን አሉኝና … ለነገሩ እኛስ ቀምሰናል ለእናነተ ይብላኝ
እንጂ አሉኝ፡፡
ይህ ግንኙነታችን የምናፍቀውን ማንነትና እውቀት ያለሰብኩት ቦታ አስገኝቶልኛልና
በጣም ተማርኩበት ደግሞም ወደድኩት፡፡ ጥቂት ሰጥታችሁ ብዙ የምትሰበስቡበት የእውቀት እርሻ ማለት አረጋውኛን ናቸው፡፡ እህ እህ
ብሎ ከሚሰማ ጆሮና ከአስተዋይ ልቦና ሌላ ምንም አይፈልጉም፡፡ ብቻ እህ በሉ ሁሉም ከዲጂታል ላይብረሪ ከተሻለ የእውቀት ክምችታቸው
በሚገርም ብቃትና ልግስና ይሰጧቸዋል፡፡
ከሁሉም ድሮ ቀረ ንግግራቸው መናፍቅም ድሮ ቀረ የሚለው በልቤ ይመላለስ
ይዟል፡፡ ምን ማለት ነው የእኔታ አልኩ አይ አስኳላ አዕምሯችሁን የት ወሰደባችሁ ግን ብለው ማወቄን በባዶነት ተኩብኝ፡፡ ብዙ የተረዳህ
ትመስለኝ ነበር ለካ ገና ነህ …. ብለውኝ ቀጭ፡፡ እኝህ ሰው የውስጥ ያውቃሉ እንዴ አልኩኝ፤ ለካስ ነገሩ አልገጥሞም ሆኖብኝ ነው፡፡
የአድማስን ያህል የተራራቅነው እኔ በማንበብ እሳቸው ደግሞ በማስተዋል መንገድ እየብቻችን ስለምንጋልብ ነው አልኩኝና ተረጋጋሁ፡፡
እሺ ይቀጥሉ አላኳቸው የኔታም ቅሬታዬን
ተረድተው ለነገሩ ጥፋተኛ እኛው ነን እንደተወለድን ትውልድን መውለድ ያልቻልን ብለው ራሳቸውን ገሰጹ፡፡ወይ ዛሬ እያልኩ ስሰማ አንድም
መናፍቅ እኮ ኣባቶቹን አያውቅም መናፍቅነትንም አልተረዳም፡፡ በጣም ይገርምሓል አንድ ቀን አንድ የእነሱ ያውቃል የተባለ ሰው ሊያገናኙን
አመጡት እኔ ሞኙ ደግሞ መቼስ የሰይጣን ትንሽ የተከራካሪም አማኝ አላገኝም ብዬ ጠዋት ለዚሁ ጉዳይ የሚሆን ሰላም ለኪ ደግሜ ጠበኩት፡፡
መጣ ሰዓት ባለማርፈዱ ደስተኛ ሆኜ እሺ መናፍቅ እንኳን በሰላም መጣህ አልኩት‹ ዋ አለኝ እንዴት መናፍቅ ይሉኛል ክርስቲያን እኮ
ክርስቲያን ነው ብሎኝ ቁጭ›
ደህና አይደለም እንዴ ሰውዬው ብዬ በልቤ ግን ከእኛ በሃይማኖት የተለዩ ሰዎችን ስም ማውጣት አንችልም አልኩት ያለሰብኩት
ርዕስ ክርክር ሆኖብኝ፡፡ በክርስቶስ ሰለምናምን አንድ ነን አለኝ፡፡ የምን አንድ አመጣህ አንድ አይደለንም ጌታን ተቀበል አልያ
ትሞታለህ(ሲኦል) ትገባለህ ብለህ ተማሪዬን መንገድ የነሳኸው አንተ አይደለህም እንዴ አለኩት፣ በዚያውስ ላይ መምሕራችሁም ባለማውቅ
ስለሆነ እንጂ መዳን ቢሰበክላቸው ቢገባቸው ይመለሳሉ አልክ አላልክም እንዴ አለኩት፡፡….. (ረዥም ሳቅ) ምን እንዳለኝ ታውቃለህ
መዳን እኮ አሁንም ቢሆን በማንም የለም … እንድንበት ዘንድ የተሰጠን አንድ እሱ…. በብዙ ትግል አቋረጥኩትና እባክህ ስምህ ማነው
አልኩት ስሙን ነግሮኝ አንድ ሰለመሆናችንና አለመሆናችን ንገረኝና ስራ ስላለብኝ ልሂድ አልኩት(አንድ ነን ካልክ አንተም እኔም አንድከም
አልኩት)፡፡ መናፍቅ ማለት እኮ ስድብ ነው አለኝ፡፡ እሺ ምን ማለት ነው አልኩት፡፡ ተጠራጣሪ ለማለት ፈልጋችሁ ነው እኛ ግን አይደለንም፡፡
ታዲያ እናንተ አማኝ ከሆናችሁ ከእኛ ክደው የምንሰብከውን የማይሰብኩ የምንቀበለውን ከፍለው የሚቀበሉ፣ የምናምነውን ሙሉውን የማያምኑ፣
ከምሥጢጢር የማይካፈሉትን ምን እንበላቸው ታዲያ አልኩት፡፡ አማኝ ሊባሉ ይገባቸዋል ትላለህ አልኩት፡፡ ድሮም ማሳደብ ነው የምትችሉት
ብሎኝ መሰስብሎ መልስ ሳይሰጥ ወጣ፡፡
እኔም በሆነው አዝኜ ባስጠራውና ባስደውልበት ጠፍቶ ቀረ፡፡ መሔዱ ቢያስከፋኝም
ልጆቼን ግን ሰላም ስለሰጣቸው ተመስገን ብዬ አለሁ ብለውኝ ተገርመው
ወደመሬት እያዩ … ግን ምን ሊያስተምረኝ መቶ ነው ምንም ሳይናገር የተመለሰው አንድ ሰው እንኳን እንደ አባቶቼ ወደ በረት ሳልመልስ
ብዬ አዝን ነበርና ሌላ ቀን ይህ በሆነ 3 ሱባዔ አንድ ራቅ ካለ ቦታ ለስራ ተቀይሮ መጥቶ ነው መጋቢያቸው ነው የተባለን ሰው ጨምሮ
ለ4 ወደ እኔ መጡ፡፡ ሲመጡ ቅድመው በለመናገራቸው ተማሪዎችን የምነግርበት ግንድ ላይ አረፍ እንዳል ሰላምታ ሰጥተው አረፍ አሉና
ያ በባለፈው ያመለጠኝ ዛሬ እጄ ሊገባ ነው መሰል ብዬ ተስፋ አደረኩና እንኳን ደኅና መጣችሁልኝ አልኩ፡፡ ያ ይዟቸው የመጣውም የወንጌል
መጋቢን አምጥቻለሁ እስኪ እሱን ያናግሩት ብሎ አምላክ ሰው ሆኖ ሊከራከርለት የመጣ ያህል ደስ አለውና ተናገረ፡፡ ለክርክር ነው
የማጣችሁ አልኩት አይ አይደለም ትንሽ ነገር ስለክርስቶስ ይነግሩን ዘንድ ነው አለኝ፡፡ አሀ አሀ አሀ ብዬ ይቺ ጭራ መወተፍ ትባላለች
አልኩና እሺ በጀ ድንቅ ነው ጸሎት ላድርስ 2 ደቂቃ ፍቀዱልኝ የምነግችሁ ባልልም የምንነጋገረው ስለ ሰማያዊ ቃል ነውና ፍቃድ መጠየቅ
ይገባል ብዬ አደረስኩ፡፡
በሉ ጀምሩ አልኳቸው ተመቻችተው እንዲቀመጡ ቤት ባፈራዉ ድርጁ መቀመጫ
እርሱዎ ይጀምሩ አሉኝ ሁለቱ በአንድ ቃል፡፡ ምኑን ልጀምር አልኳቸው እናንተ ጠይቁ ልመልስ አልያም ርዕስ ስጡኝ እንጂ አለኳቸው፡፡
አይ የለም እርስዎ እያሉማ ብለው ችክ አሉ፡፡ ከባለፈው ትምህርት ወስጄ እነሱን ከነሃሳባቸው ለማወቅ መናፍቅ ላለማለት ተጠነቀኩና
እሺ መቼስ እምቢ ካላችሁ ብዬ የሃይማኖት አባቶቻችሁ/ዋኖቻችሁ/ እነማን ናቸው አልኳቸው፡፡ ለመዳን ይኤ አያስፈልግም አሉኝ፡፡ መጋቢ
እርስዎ ዋና የሚሉት መምህር አሰረ ፍኖቱን የተከተሉት የሎዎትም አልኩ፡፡በምድር ላይ ያለክረስቶስ መምህር ሊባል የሚችል የለም አለኝ፡፡
አሁን ነው ጨዋታ አልኩና የጳውሎስ ትዕዛዝስ አልኩት፤ አይ ለመዳን የሚያስፈልገው እኮ በክርስቶስ ማመን ብቻ ነው አለኝ፡፡ ወይ
ጉድ ምን ሰው ነው የገጠመኝ አልኩና የእኔን ጥያቄም ላለመመለስ የእኔን መልስም ላለመስማት እንደው ተናግሮ ለመሄድ መምጣታቸውን
ያወኩት ያለ መሪ እዛም አዛም ሲቀበጣጥሩ ስመለከት ነው፡፡
መጋቢ ለመሆኑ ሃያማኖት አሎዎት አልኩኝ በሚገባ ጌታ ኢየሱስ ብቻ ያድናል
የምትል አለኝ፡፡ መቼ ተጀመረች አልኩት፡፡ እሱ በምድር ላይ ሲያስተምር ጀምሮ የነበርች ናት…. አለኝ፡፡ከዚያስ ሌላ ማን አስተማራት
ከአንተ በፊት ሐዋሪያት ብዙ አማኞች እየተፈራረቁ
አስተምረዋታል አለኝ፡፡ በጣም ጥሩ ታዲያ ዋነኞች አሉህ ማለት ነው፡፡ አዎ እነማን ናቸው አልኩት፡፡ ቅድም የጠቀስኳቸው አለኝ፡፡
ሉተር ምንህ ነው አልኩት አንድ አማኝ(መስካሪ) ነው አለኝ አፉን ሞልቶ፡፡ ስለዚህ እሱ ትክክል ነበር አልኩት አስከትዬ አዎ በሚገባ
እንጂ ቀድሞ ግን ስህተት ውስጥ ነበረ አለኝ፡፡ ስለዚህ አንዱ ዋነኛህ እሱ ነው ማለት ነው አልኩት እየተቁነጠነጠም ቢሆን አዎ አዎ
አለኝ፡፡ አርዮስስ አልኩት ከሀዲ ይመስለኛል ግን አላውቅም በሰዎች ዐይን ያለውን ጉድፍ… ብሎ ቀጠለ፡፡ ከአብና ከወልድ ሎቱ ስብሓት
አብ ይበልጣል እሱ ፈጣሪ ሲሆን ወልድ ደግሞ የመጀመሪያ ፍጥረትና በእሡ ዓለም የተፈጠረበት ነው ይል ነበር አልኩት፡፡ እና ና ልክ እኮ
ነው ስልጣንን ሁሉ ለልጁ እስኪሰጠው ድረስ ተብሎ ከሁሉ እንደ ታናሽ ተቆጠረ ይል የለ እንዴ አለኝ፡፡ ስለዚህ አልኩት አብ በአምላክነትና
በሰጪነት ያበልጣል ማለት ነው አዎ ብሎ…….(የጥቅስ መዓት ዘበዘበብኝ)፡፡
ለመጠቅለል ያህል ግን አርዮስ ይህን አመለካከቱን ትደግፉታላችሁ አልኩት አይ እሱ እኮ ከሀዲ ነው አለኝ፡፡ ምን ብሎ
ካደ አልኩት ዝምምምምም አለኝና ቆይቶ ስለ ቅዱሳን አማላጅነት አናውራ አለኝ፣ እንዴ በዚህ ተስማማን
እንዴ አልኩት አይ ችግር የለም ካልሆነ እንመለሳለን አለኝና ሊጀምር ሲል፡፡ ወይ መጋቢ ስለ መድሓኒቱ መድሓኒትነት ሳንግባባ ስለመድሓኒቱ
መያዣ ምን አዳረቅን አልኩት፡፡
ንስጥሮንስ ታውቀዋለህ
አውጣኪንስ
…… አይ አላውቃቸውም፡፡ አለኝና እነዚህ ነገሮች ለመዳን አያስፈልጉም አለኝ፡፡ ዋ ታመሃል እንዴ ሃይማኖትን እኮ
መጀመር ኤቻልም ማስቀጠል እንጂ አልያማ እግዚአብሔር ባለዕዳ ነው ከዛ ትውልድ ለይቶ አንተን ብቻ እንድተድን ይህን ሃይማኖት ገልጦልሃልና፡፡
በዛውስ ላይ የሲኦል ደጆች አያናውጧትም የታባለውስ ወዴት አለ መፈጸሙ በአንዱ ዘመን ሳትኖር በአንዱ ዘመን የምትኖር ሃይማኖት ከሆነች
አልኩት፡፡ አባት የሌለው ልጅስ ምንኛያልታደለ ነው ባክህ መጋቢ ብዬ አልኩት፡፡ መልስ ባይሆኑም ብዙ ጥቅስ እንዳነበበ ብቻ ለማሳወቅ
ሞከረ እንጂ ለእኔ ውሃ አልቋጠረልኝም፡፡ አንተ ሰው ወደኋላ ሳያዩና
ሳይንደረደሩ ወደፊት ብዙ ርቀት መዝለል እንኳን በሃይማኖት በዓለማዊ ዘላዮችም አይቻልም አልኩት፡፡ ጥሩ መንፍቅ ለመሆን እንኳ ብታስብ
አባት ሊኖርህ ይገባል ታሪክ ልትጠይቅ ይገባል አልኩትና ግን መጋቢ በቃ በዚህ ነው ትውልዱን በአዳራሽ ያከማቻችሁት
በቃ በዚህ ነው ትውልዱን አዚም ያደረጋችሁት… አልኩና ከልብ ማዘኔን ገለጬለት በል ወንድሜ ወንድሞቼን በማሰናከልህ
እንዳትጠየቅ ቢያንስ ቀድመው የተጠየቁትን ብትር አድርጋቸውና ስታውቅ እንተዋወቃለን ብዬ ተለየሁት››››››› በዚህ ሁሉ ግን የገረመኝ
ወይ ስንቱ መናፍቅ እንዳልበቀለባት ዓለም አሁንማ መክናለች መች ወለደች፡፡ እኛም እንሱም የእሳት ልጅ አመድ ሆነናል ለካ፡፡ ምን
መናፍቅ አለ ይልሃል ይሄ ነው አሉኝና ምን መናፍቅ አለ
መናፍቅም ድሮ ቀረ…….
እነሱ ከሚያውቁት በላይ እኛ ስለእነሱ እናውቃለን፣ ታዲያ መመጣጠን ከወዴት ይምጣ፡፡እረ እኛ አለን መናፍቅ አዲስ
ርዕስ ለመከራከሪያ የሚበቃ አለን የምትሉ ካላችሁ ሀሣባችሁን አምጡ እንከራከር፡፡
መቼም ልጆቻችሁ ከእናንተ እንዳይወጡ ስለምትፈልጉ ወይ አባቶቻችሁን ንገሩን ቀድሞ እንደተወገዙት እናውግዛችሁ አልያም
አዲስ ሃይማኖት ነው፣ ጌታ ከዓለም ለይቶ ለእኔ ብቻ የገለጠው እኔን ብቻ ለማዳን ነው በሉኝና ልረፈው አሉኝ፡፡
ወይ እይታ ብዬ …… ከልቤ ተደንቄ አመሰገንኩ….. እኔ ስንት ጥቅስ ለማበላሽበት ክርክር መልሱ ለካ በራሱ መናፍቁ
ምላስ ላይ ኖሯል፡፡
በርታ አሉኝ ሌላ የጨዋታ ርዕስ አስጀምረውኝ ቀጠልን፡፡
ይቀጥላል! ጊዜ ከተገኘ፡፡!!! ፳፩፣ ፳፻፯ ዓ.ም.
Comments