Refusal decision of the Holy synod members of Ethiopian orthodox church about Reformist/Tehadiso/Hara tiqa/ service in the name of the church
አሁን እነዚህን አባቶቻችንን ምን እንበላቸው??? የዚህ ጽሑፍ ዋና ዓላማ ልጆቻቸውን በትዕግስት ሰምተው፣ እውነትነትን አጣርተው፣ የእግዚአብሔርን ፍቃድና ፍርድ ለቤተክርስቲያን ያስተላለፉትን የዘመናችንን ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ክቡራን አባቶቻችንን ማበርታትና በዚህም በረከታቸውን ማግኘት ነው፡፡ አሁን ያለንበት ዘመን በጎ አይሉት ክፉ፣ ክፉ አይሉት በጎ ሆነና ብዙ ይነገራል፣ ብዙ ይሰማል፣ ብዙ ይጻፋል፣ ብዙ ይነበባል፣ ብዙ ይታያል ጥቂቱን ግን እንመለከተዋለን፡፡ በተለይም በዚህ ዘመን ላይ ላለን ትውልዶች ፈተናም ካወቅንበት መልካም አጋጣሚም የሚሆኑ በርካታ ነገሮች(ክስተቶች) አሉ፡፡ ለዛሬው ግን የተሃድሶን ስልትና እንቅስቃሴን ማሰቡ በቂያችን ነው፡፡ ምክንያቱም በዚህ አንድ ዘመኑ ክስተት · ብዙዎች ተጠቅመዋል፡፡ 1. በመንፈሳዊ ምዘና ሲታይ አባቶቻችን ከቀድሞው እስከ አሁን በውሳኔያቸው፣ በተለይም በሰሞኑን የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ፍሬው ያማረ ውሳኔ፤ አገልጋዮቻች ብዙዎች እንዲነቁ ተግተው ሰርተዋል፤ በጽሑፍ፣ በስብከት፣ በጸሎት፣ በክርክርም፣ በውግዘትም ሳይቀር የሚችሉትን ለማድረግ ወስነዋል…. ስለዚህም ተጠቅመዋል፡፡ 2. በስጋዊና ግዑዝ በሆነ ምዘና ደግሞ በገንዘብና ተከታይ ድሆች የነበሩ አሁን ቢጠሯቸው አይሰሙም፣ ታዋቂ ያልነበሩ ለብዙዎች መውደቅና መሳት ምክንያት ሆነዋል ባይዘልቅም እስካሁን ግን ብዙ ደጋፊና ወዳጅ አፍርተዋል፡፡ከሞትህ በፊት እኔ ልሙት የሚሉ ባለማስተዋል የሚንቀሳቀሱ አጃቢዎችን አፍርተዋል፤ የሚበዙትም በስደት የሚገኙ ምዕመናን ናቸው፡፡ § እናታችንን...