በስራው አንተ ያልኩትን ፓትርያርክ መልሼ አንቱ እለው ዘንድ ጸሎቴ ነው፡፡
ጠላት የሆነን (ያዕቆባዊ ኤሳውነት)ፓትርያሪካችን ነው፡፡ እንዴት ቢያነስ ችግራችንን ላለመፈጠሩ ትብብር አለማድረግ ቢያቅተው ችግሩ እንዲፈታ ትብብር አያደርግም፣ እንዴትስ የቅንነት መንፈስ ቢያጥረው የትዕቢትና የበቀል መንፈስ ሰለጠነበት፣ ከዚህ ወዲያ ወድጄ ሳይሆን ተገድጄ አንቱ ማለቴን ትቻለሁ፡፡ ግን በሞቴ ምን አንድነት አለን? ምንም፡፡ እውነት እላለሁ ማኅበሬ በትክክል ዓለም እንዳልተገባውና ሀገሩም እዚህ አለመሆኑን በተግባር ተረዳሁ፡፡ እሰኪ ማነው የተገፋ? እስኪ ማነው የተናቀው?... እውነት እላለሁ እኔ ዮሴፍን ከሚሸጡ ጋር ዝምድና የለኝም፣ ሕልመኛውን ቀበሮ ጉድጓድ ከሚከቱ በረከት አልሻም፣ ግን ርሃብ ሲመጣ(ሲጸናባቸው) አስጠጋን ማለታቸው አይቀርምና ርሃብ እንደያዛቸው እንዳይሞቱ ሕልሜን ልንገራቸው፡፡ አንተ ዮሴፍ የቤተክርስቲያን ሕልመኛ መተዳደሪህ ደንብህን(መኖርህን) የሚጠሉ የበዙብህ የአንተ የሆኑት አሳልፈው ሊሰጡህ የሚጓደዱብህ በረከት ፈላጊዎች ግን የሚንከባከቡህ፣ የሚሳሱልህ ገና በእስር(በምስረታህ) እያለህ የሚሆኑትን አስቀድመህ የምትናገር ተኩላን ለማባረር የአቅምህን የተወጣህ እየተወጣህ ያለህ .…ሰላም እልሃለው፡፡…ሰላም እልሃለው፡፡.. ሰላም እልሃለው፡፡ አብሬህ ሆኜ እን...