
+ እንኳን ለጌታችንና ለመድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ልደት በሰላም አደረሳችሁ!!!+ ለሚገባችሁ ና ለሚገባች ጓደኞቼ በሙሉ_____________________________________________ 1 ኛ ዩሐ 4 ÷ 9 “በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና፡፡” ይህ የሆነው እከብር አይል ክቡር፣ እነግስ አይል ንጉስ፣ ቅድመ ዓለም የነበረ፣ ማዕከለ ዓለም ያለና ድህረ ዓለም የሚኖር ሁሉን በፈቃዱ የሚያከናውን የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ በቤተልሔም ሲወለድ ነው፡፡ ከዚህ ፍቅረ እግዚአብሔር መገለጥ በፊት ብዙ አባቶቻችን በምግባር ቢቀኑም ብዙ ነቢያቶችም በትንቢት ቢተጉም ይህን የተከበረ የአምላክ ሰው መሆን ምስጢር በምሳሌና በትንቢት መነጽር አይተውታል እንጂ አልደረሱበትም ፤ ‘’እኛ ግን ዳሰስነው፣ አብረነውም በላን፣ ጠጣን… ይህን የተመለከቱ አይኖቻችሁ፣ ይህን የሰሙ ጆሮዎቻችሁ ብጹዓን ናቸው’’ እንደተባለ፡፡ ይህ የአምላክ ሰው መሆን ልዩ እና ታላቅ ፍቅር ለሰው ልጅ የተገለጠው በእግዚአብሔር በጎ ፍቃድና በሰው ልጆች ሁሉ አባት አዳም ንስሐ መግባት ምክንያት ነበር፡፡ የመገለጡም ዓላማ v ኃጢአትን መሻር ዕብ 9 ÷ 26 ዩሐ 3 ÷ 16 v የአዳምን የቀደመ ክብሩን መመለስ ገላ 4 ÷ 7 v ለአዳም ልጆች ምሳሌ ሊሆነን ብሎ ዳግማዊ አዳም ከርቀት ወደ ግዝፈት፣ ከምልዑነት ወደ መወሰን መጥቶ የተሰወረ የመለኮትን ነገር አሳወቀን፡፡ ማቴ 3 ÷ 16፣ የጨለማ ዘመን ያበቃባት ብርሃን የተገለጠባት ያች የኤፍራታ አውራጃ ቤተልሔምም ቅዱሳን መላዕክትና ሕጻናት በአንድ ቃል የጥል ግድግዳ መፍረሱን ...