እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክረስቶስ የልደት በዓል አደረሰን አደረሳችሁ!!!
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!! ፩ኛ ጢሞ ፩ ፥፲፭ “ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ” ቅዱሳን አባቶቻችን እንደመሰከሩልን የእግዚአብሔር ዓለምን ማዳን ዓለምን ከመፍጠሩ ይደነቃልና ስለዚህ ተወዳጅ እና ሁላችን ተስፋ ስላገኘንበት የጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ፡፡ በዚህ ጽሑፍ የሚከተሉትን ቁምነገሮች እናገኝበታለን፡፡ v አምላክ መቼ፣ እንዴትና ለምን ሰው ሆነ› v ሰው በመሆኑ ማን ተጠቀመ ማንስ ተጎዳ v የሰጠን ድህነትስ እስከምን ድረስ ነው፡፡ በዚህም መሰረት እያንዳንዱን አምላከ ቅዱሳን በረዳን መጠን በዝርዝር እንመልከት፡፡ v አምላክ መቼ፣ እንዴትና ለምን ሰው ሆነ ያን ጊዜ በክብር ሳለን በእርሱ እቅፍ ከነሞገሳችን ሆነን የጥንት ጠላታችን ዲያበሎስ ምክንያተ ስሕተት ሆኖ ከክብር፣ ከማዕርግ ና ከሞገሳችን እግዚአብሔር ለይቶ የመከራ ፍድ አመጣብን፡፡ ለሰው ልጅ መሳሳት ሌላ ውጫዊ ምክንያት መዘርዘር አዋጪ እንዳልሆነ በዚያን ጊዜ በተፈፀመው የእውነት ፍርድ ተመልክተናልና፣ ስለዚህም ዛሬም ሆነ ቀድሞ ለስህተታችን የጎላውን ድርሻ መውሰድ ያለብን እኛው እራሳችን ነን ምክንያቱም የተሰጠንን ኃላፊነት በአግባቡ ስላልተጠቀምንበት ነው እንጂ ክፉ ስራ(ኃጢአት) እኮ ካልነኳት አትነካም፡፡ ሆኖም ግን አክብሮ የፈጠረን እግዚአብሔር ለውርደትና ለሲኦል አልነበረምና አዳም አባታችን በቃረበው አውነተኛ መስዋዕትና ጸሎት የጠብ ግድግዳ የሚፈርስበት የዕዳ ደብዳቤ የሚቀደድበትን እለትና ሁኔታ አመላከተው፡፡ ይህም በመልዕክተኛ ሳይሆን ራሱ “አዳም አዳም ወዴት አለህ” ብሎ ተስፋ በቆረጥንበ...