መናፍቅም ድሮ ቀረ ልጄ???
መናፍቅም ድሮ ቀረ ልጄ??? በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን! እኔ ግን እላሉሁ · ስም ድሮ ቀረ! እነ እሱያውቃል፣ ተስፋነሽ፣ ግሩም፣ እጹብድንቅ፣ ተመስገን፣ …. እረ ስንቱ ምንጥ ስም እንሰማ ነበር አሁንማ ምን ስም አለ….(ያለ ምክንያት ቲቲ ዳዲ ሪች…. ከመባል ውጭ)፡፡ · ምግብ ድሮ ቀረ፣ መዝናናት ድሮ ቀረ፣ ምንኩስና ድሮ ቀረ፣ ብሕትውና ድሮ ቀረ፣ አባትነትም እናትነትም ድሮ ቀረ፣ መምሕርነት፣ ተማሪነት፣ መሪነት ተመሪነት ሁሉም ተያይዘው ድሮ ቀሩ …. (በቃ ሁሉም ድሮ ቀረ ብለው በባሕል፣ በወግ መጣስና መጠበቅ አለመቻል ሆድ እየባሳቸው አንድ ሊቅ ነገሩኝ)፡፡ · ሌላው ቀርቶ ለማኝነትም ድሮ ቀረ …አሁንም ፈሽን ተከታይ ለማኝ ሀገሪቷን ወሯት አይታይህም አሉኝ፡፡ ... ምን ማለትዎ ነው ስላቸው እነዲህ አሉኝ እስኪ ስማው የሚለምንበት አላማን የሚለምንበት ስምና መንገድ ልመናውን ጨርሶ ሲሳካለት የሚያመሰግንበት መንገድና ቃላት…. (እኮ ፍጹም ኢትዮጵያዊውም ሃይማኖታዊም ሽታ የላቸውም… ዝርዝሩን ለአንተ አሉኝ)፡፡ · ግን እኮ….. መናፍቅም ድሮ ቀረ ብለውኝ እርፍ አሉ፡፡ እናንተ ለካ መናፍቅ/ ኢ አማኒም የለም/ አሉኝ …… ወቸ ጉድ ብለው እኛን በክርክር አላስወጣ አላስገባ ያለንን ይህንን ሁሉ መሰረተ ቢስ መናፍቅ ወዴት ዘነጉት እንድል አደረገኝ፡፡ ለነገሩ አሉኝ እግዚአብሔር ላያስችል አይሰጥም ይባላል አሉኝና የተለመደው...