ይድረስ፤ ለሰማዕታት፣ ለአባቶችና ለቄሳሮቻችን
ይድረስ ለእናንተ ሰማዕታት ለጤናችሁ እንደምን አላችሁ እንዳልል ሰላም ከሌለበት ዓለም በሰላም አባት ክርስቶስ መጠራታችሁን መሪዎቻችንና አባቶቻችን በይፋና በፍጥነት ባይነግሩንም ጠላቶቻችን ገዳዮችና ባዕዳኖች የተባሉ መገናኛ ብዙሃን ነግረውናል፡፡ እናንተየ አዲሱ ቤታችሁ እንዴት ያምር? እንዴት ይደንቅ ይሆን? እንዴትስ የሚያብረቀርቅ የተወደደና የተለየ ዘላቂ ማረፊያ አግኛታችሁ ይሆን? እኔ ምለው ሰማዕታት ለመሆኑ ማነው ያስተማራችሁ? ማነው ያጠመቃችሁ? ማነው ያሳመናችሁ? ማንስ ነው የሰማዕትነትን ዋጋና ጣዕም ያቀመሳችሁ? ማንስ ነው ዘመኑን አትምሰሉ፣ ወደኋላ አትበሉ፣ የሎጥን ሚስጥ ታሪክ አስታውሱ ያላችሁ? ማንስ ቄስ ፣ ማንስ ጳጳስ ትጉ በርቱ ጽኑ ብሎ ቡራኬ ሰጣችሁ? የትስ ኮሌጅ ፣የት ዩኒቨርስቲ የመንፈስ መበርታትን የዓላማ ፅናትን ተማራችሁ …….. ? መልሱን ለውሳጣዊ ነፍሴ መልሱላት(አማልዱኝ)፡፡ እኔ ግን እላለሁ እናንተ ሰማዕታት ንዑዳን ናችሁ, ገንዘብ ብላችሁ ሄዳችሁ ሐይማኖት ገዝታችሁ መጣችሁ, ላንረሳ በልባችን ተፃፈ ስማችሁ እናንተ ሰማዕታት ክቡራን ናችሁ, ኢትዬጵያ ሀገረ እግዚአብሔር መሆኗን ለዓለም መሰከራችሁ፡፡ ...