Posts

Showing posts from November, 2014
Image
የሀና ደፋሪዎች ከየት መጡ!? የሚከተሉት ሰዎች እህታችንን የምድር ቆይታዋን ቀጩባት ያሳዝናል፡፡ ሀና ፍርድ በዚያ አለ፣ እውነት በዚያ አለ፣ አምላካችንም መልክ፣ ስልጣን፣ ቁመና፣ ገንዘብ፣ ዝና …. ሌሎችም ሁሉ ለፍርዱ የማይጠቀም ነውና ፍርድ ታገኛለሽ፡፡ ይሁን እንጂ እኚህ ክፉ አውሬዎች ጨከኞችና ከሀዲዎች ያደረሱብሽን ባልናገር ከበደኝ እናም ላጋልጣቸው ተነሳው፡፡ እኔ ምለው አንተ አንባቢ ደሞ ለምን፣ ማን፣ እንዴት ተደፈረች ትላለህ/ሽ/ ? አታፍርም እንደማያውቅ ሰው ታስመስላለህ ? ግፍ አይሆንብህም፣ ህሊና አልህ ግን ? ስማኝ ልጠቁምህ ሀናን የደፈራትን ያዋረዳትን ያን ሰው መሰል ፍጡር፣ ሰው ነኝ ባይ ፍጡር አውቀዋለሁ/አውቃቸዋለሁ/ አውቅሃለው፡፡ እኔ ግን እላለሁ እነዚህ ደፋሪዎችና ሰው ብቻ ሳይሆን እንሰሳም መሆን ያቃታቸው፣ ኢትዮጰያዊ ያውም ጎረቤቶቻችን እነ እንትና/እነ እገሌ/ ናቸው፡፡ ለማስለፍለፍ ፈልጋችሁ ካልሆነ እናንተ አንባቢያኖች ሁላችሁም ታውቓቸዋላችሁ እረ እንደውም እናንተም ራሳችሁ ተባባሪ ነበራችሁ አውቃሁ፡፡ የማላውቅ መስሏችሁ እንጂ አውቃለሁ፣ ያልሰማው መስሏችሁ እንጂ ሰምቻለው፣ ያላየው መስሏችሁ እንጂ አይቻለው፡፡ መቼስ የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያድርቅ አይደል የሚባለው፤ ከዘበዘባችሁኝማ አውነቱን ላወጣ ነው፣ እውነተኛ ዳኛ ይዳኘን ብዬ፡፡ ለነገሩ ፍርዱም የተበላ ዕቁብ ሆኗል አሉ፣ ራስን የማያውቅ ዳኞች ናችሁ አሉ፣ እውነትን ሳይሆን ክብርን፣ ገንዘብን፣ መወደድን፣ ስልጣንን….. የምታሯሩጡ ቀማኛ ናችሁ አሉ፡፡ እናም ልንገራችሁ እንጂ እናንተስ ፍርድ አታውቁም፣ ፍርዳችሁም ኦርዮን እንዲገደል መሆኑን አውቃለሁ፡፡አይ አንተ ኦርዮን ሚስትህንም፣ ፍቅርህንም፣ ህይወትህንም የተነጠክ ምንኛ ፍርድ ተጓደለብህ ??? ፍርድ ...